ዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ICRC ሳይበር/cyber የደህንነት ችግር

 

በቀን 18 ጥር/January 2022 ዓ.ም የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል (ICRC) ኮሚቴ በራሱ የመከታተያ ሳይበር-ጥቃት አድርጎ እንዳወቀ፤ ይህም ባልታወቀ ሳይበር የተራቀቀ ተዋናይ (ከቀይ መስቀል ውጭ የሆነ ሰው) ለተቀመጠ የቤተሰብ መርበብ (RFL) ጥሬ መረጃ አግንቶ መጠቀም።

በቀን 20 ጥር/January 2022 ዓ.ም የአውስትራሊያ ቀይ መስቀል ችግሩን አሳውቋል።

አዲስ መረጃ በሚቀርብበት ጊዜ በዚህ ገጽ ላይ በተከታታይ ወቅታዊ የሆኑትን መረጃ እናቀርባለን።

ተጨማሪ እርዳታ ወይም አስተርጓሚ ከፈለጉ፤ እባክዎ ለእኛ መስዋት ያደረገ በቀን 24 ሰዓታት በሳምንት 7 ቀናት ሆትላይን መስመር ይደውሉ፤ በስልክ 1800 860 442

ለዓለም አቀፍ ስልክ ጥሪዎች፤ እባክዎን በዚህ ስልክ ያነጋግሩ +61 2 8077 2507

ስለ ዓለም ዓቀፍ ቀት መስቀል/ICRC ሳይበር የደህንነት ችግር

ምን ተፈጠረ?

የICRC አጣርቶ እንዳገኘው ከቀይ መስቀል ወይም ቀይ ሩብ ጨረቃ እንቅስቃሴ (RCM) አገልግሎት ለሚያገኙ ከ500,000 በላይ ለሚሆኑ ሰዎች በግላዊ መረጃ ለተደረገ የመከታተያ መስተንግዶ በተራቀቀ ሳይበር የደህንነት ጥቃት ላይ ድርድር ተካሂዷል። የአውስትራሊያ ቀይ መስቀል ይህንን ጥሬ መረጃ ለእኛ RFL እና እስር ቤት መቆጣጠሪያ ፕሮግራም ይጠቀማል። መረጃው በአውስትራሊያ ቀይ መስቀል ወደ ጥሬ መረጃ ማስቀመጫ በተለይ ችግር በፈጠረው ውስጥ ስለመግባቱ እስካሁን አናውቅም። የቀይ መስቀል ወይም የቀይ ሩብ ጨረቃ ቡድኖች በዓለምአቀፍ ያለን መረጃ ማስቀመጫን ይጠቀማሉ፤ ይሁን እንጂ መረጃው በማስቀመጫ ላይ የሚቀመጠው ከምንሰራበት ማንኛውም ጉዳይ፤ ከማንኛውም አገር የመጣ ነው።

ለአውስትራሊያ ቀይ መስቀል ያቀረቡት መረጃ በመረጃ ማስቀመጫው ላይ ሊቀመጥ ይችል ይሆናል። መረጃውን በአንድ ቦታ እንዲቀመጥ ለማረጋገጥ ይህ መደበኛ የአሰራ ሂደት እንደሆነ እናም አንድ ለጠፋ የሚወዱትን ሰው ለመፈለግ ሲሞከር በሌላ አገሮች ካሉት የስራ አጋሮቻችን ጋር መገናኘት እንችላለን።

በዚህ መረጃ ውስጥ ሊካተት የሚችለው የእርስዎ ስም፤ ዝርዝር መረጃ አድራሻ፤ ስለጠፋው የሚወዱት ሰው ሁኔታ እና ስለነገሩን የማንኛውም ዘመድ ስምና ዝርዝር መረጃ አድራሻ ወይም ከእኛ ጋር ለጠቀሱት ስለ የርስዎ መታሰር እና አሳሳቢ ሁኔታን ይሆናል። የርስዎን ጉዳይ በምናቀናጅበት ጊዜ ላቀረቡልን ሰነዶች በሙሉ ያካትታል፤ ይህም ለማንነት መታወቂያ ሰነዶች፤ ለተሞሉ ቅጾች፤ ከICRC የመታሰር ምስክር ወረቀት ማረጋገጫ፤ በቤተሰብ አባላት መካከል ለተደረገ መልእክቶች መለዋወጥ እና ፎቶዎችን ሊያካትት ይችል ይሆናል።

በአሁን ጊዜ ስለ ግላዊ መረጃዎ መሰረዝና ለመክፈት ሙከራ መደረጉ የሚያሳይ ምንም መረጃ እንደሌለ እናሳውቃለን። ከዚህ በበለጠ ለዚህ ጥሬ መረጃ ያላግባብ መጠቀም ወይም ለህዝባዊ መውጣቱን የሚያሳይ ምንም ዓይነት ማስረጃ የለንም። ይህ በቅርበት ግምገማ እንደሚደረግበትና ታዲያ ይህ ሁኔታ ከተለወጠ እናሳውቅዎታለን።

ለተፈጠረው ችግር ሁኔታ ምላሽ ለመስጠት ምን ተደረገ?

ችገሩ ስለመፈጠሩ የICRC ሲያውቅ በፍጥነት ማቅረቢያው ከመስመር ውጭ እንዲዎን በድርድር ተስማምተዋል። ይህ ማለት በአሁን ጊዜ ለማንኛውም ጉዳይ መረጃ ወይም በማንኛውም ጉዳይ ሥራ ላይ መጠቀም አንችልም።

በዚህ ሁኔታ ችግር ለደረሰባቸው ሰዎች የሰብአዊነት አገልግሎቶችን በቀጣይነት ለማቅረብ፤ በሞላው ዓለም ባሉት የቀይ መስቀል እና ቀይ ጨረቃ ቡድኖች የአጭር ጊዜ መፍትሄ ለመለየት አሁን ICRC በአሰራር ሂደት ላይ ነው።

በተናጠል፤ እነዚህ ሰዎች በደህንነት እንዲቆዩ ለማድረግ የአውስትራሊያ ቀይ መስቀል በአካባቢ የአሰራር ዘዴዎችና አገልግሎቶች ላይ ተጽእኖ በሌለበት የራሱን ግምገማ ያካሂዳል።

በጋራ በመሆን፤ ጉዳት ለደረሰባቸው ደንበኞች ለመርዳት እና ተመሳሳይ ችግር እንደገና እንዳይፈጠር ለመከላከል በበለጠ የአሰራር ዘዴን በማጠናከር አብረን እየሰራን ነው።

ለምንድ ነው የምናነጋግርዎት?

የምናነጋግርበት ምክንያት ከዚህ በታች ባሉት አገልግሎቶች በአንዱ ወይም ከዚያ በላይ ጋር በተያያዘ ከእርስዎ ጋር ስለሰራን ነው:

  • በጦርነት፤ በአደጋ ወይም በስደት ምክንያት ለጠፋ የቤተሰብ አባል ስለማፈላለግ።
  • ምንም ዓይነት ሌላ የመገናኛ መንገድ ከሌለ ለዘመድ መልእክቶችን ስለመላክክ።
  • በውጭ አገር ማግኘት ላልቻሉት ዘመድ በበጎ አድራጎት ስለማጣራት።
  • ስለ ግለሰቡ ሰነዶችን ስለመጠየቅ።
  • የኢሚግሬሽን የማቆያ መገልገያ ሁኔታዎችን ስለመቆጣጠር ነው።

እንደ ችግሩ ያመጣው ውጤት፤ በዚህ አሰራር ሂደት ጊዜ በእርስዎ ወይም በሚወዱት ሰው የቀረበ አንዳንድ መረጃ ችግር ሊፈጠርበት ይችል ይሆናል። እባክዎ በዚህ ችግር ለደረሰበት ማንኛውም ተወዳጅ ሰው ማነጋግር ይህም ላያውቁ ስለሚችሉ ነው።

የRFL ጥሬ መረጃ ማስቀመጫ ምንድ ነው?

የRFL ጥሬ መረጃ ማስቀመጫ የሚጠቅም በዓለም ዙሪያ ባሉት አውስትራሊያ ቀይ መስቀልና ቀይ ሩብ ጨረቃ ሕብረተሰባት ሲሆን:

  • ለጠፋ ሰው ማፈላለግ ለመርዳት
  • ስለ RFL ጉዳዮች መረጃ ለማካፈልና ለማስቀመጥ፤ ይህም በሌላ አገር ካሉት ዘመዶችዎ ጋር መልእክቶችን መለዋወጥ ያካትታል።
  • በኢሚግሬሽን ማገቻ ውስጥ ላሉት ሰዎች በእኛ በኩል የተነሱትን የሰብአዊነት ጉዳዮች ሪኮርድ ለማድረግ
  • በኢሚግሬሽን ማገቻ ውስጥ ላሉት ሰዎች የሚደረግን ግንኙነት ማስቀመጥ።
  • ለእርስዎና ቤተሰብዎ ለመርዳት ወደ ሌላ አካል ስለመላክ የቀረበን መረጃ ሪኮርድ ማድረግ (ቀደም ብሎ ከርስዎ ጋር በተወያዩበት)።

የRFL ጥሬ መረጃ ማስቀመጫ የሚቀመጥ ጀነቫ ውስጥ እንደሆነና የ ICRC ቁጥጥር ያደርጋል።

ለምንድ ነው ICRC የእርስዎን ግላዊ መረጃ ያለው?

እንደገና ስለሚቀመጥ የቤተሰብ መርበብ (RFL) በሞላው ዓለም ላሉት አገሮች የሚደርስ ዓለምአቀፍ አገልግሎት ነው። የአውስትራሊያ ቀይ መስቀልን ያካተተ ቀይ መስቀልና ቀይ ሩብ ጨረቃ ሕብረተሰባት ስለ RFL ጉዳዮች መረጃን ለማስቀመጥ በኦንላይን አሰራር ዘዴ ይጠቀማሉ። እኛ ይህን እናደርጋለን ታዲያ መረጃን ደህንነቱ በተጠበቀ አንድ ቦታ ማስቀመጥና ለጠፋ የሚወዱት ሰው ለመፈለግ ሲሞከር ከእኛ የቀይ መስቀል አጋሮቻችን ጋር ግንኙነት ማድረግ እንችላለን።

እንዲሁም በኢሚግሬሽን መቆያ ውስጥ ላሉት ሰዎች በሚረዳበት ጊዜ ይህን የአሰራር ዘዴ እንጠቀማለን።

ምን ዓይነት ግላዊ መረጃዎ ነው ችግር የተፈጠረበት?

በRFL ጥሬ መረጃ ማስቀመጫ እና ከዚህ ጋር በተያያዙ አሰራር ዘዴዎች የICRC መከታተያ ማስተናገጃ በስምምነት የተደረገ ነበር። አጭበርባሪ ጠላፊዎች በአሰራር ዘዴው ውስጥ እንደነበሩና ታዲያ መረጃን የማሸጋገርና መቅዳት ችሎታ አላቸው። በአውስትራሊያ ቀይ መስቀል በኩል ወደ RFL ጥሬ መረጃ ማስቀመጫ የገባው መረጃ፤ በተለይ ችግር የፈጠረው ትክክል ስለመሆኑ እስካሁን አናውቅም። ችግር መፍጠር በቻለው መረጃ የሚካተት ስለ ጕዳይዎ በተደረገ ንግግር ለውጥ እና ሪኮርድ፤ ይህም በጉዳይዎ ላይ ጠቃሚ ከነበር ለሚወዱት ሰው የመገናኛ ዝርዝር መረጃን ያካተተ ይሆናል። እኛ በምናውቀው መረጃው እንዳልታተመ ወይም በዚህን ጊዜ እንዳልወጣና እኛ በቅርበት እንቆጣጠራለን።

እራስዎንና ግላዊ መረጃዎን ለመከላከል ምን ዓይነት የጥንቃቄ እርምጃዎችን መውሰድ ይችላሉ?

የመገናኛ ዝርዝር መረጃዎን ሶስተኛ አካል ማግኘት ስለሚችል፤ ለሚከተሉት ማድረጉ ጠቃሚ ነው:

  • ፓስዎርድ/passwords መቀየር – እስካሁን ካላደረጉ በኦንላይን ያለዎትን ፓስዎርድ/መግቢያ ቃል መቀየር። እንዲሁም የእርስዎን ፓስዎርድ/መግቢያ ቃል በኢሜል አድርገው ወደ ሌላ አካውንት ልከው ከነበር መቀየር። የአውስትራሊያ ሳይበር ደህንነት ማእከል ጥሩ የሆነ ስለ ፓስዎርድ/password አሰራር መመሪያዎችን ያቀርባል።
  • ጥንቃቄ ማድረግ – በወብ/ድረገጽ አድራሻ ላይ ጥርጣሬ ካለዎት ትክክለኛ ገጽን ስለመክፈትዎ ለማረጋገጥ የአገልግሎት አቅራቢዎን ማነጋገር። የርስዎን ተጭኖ መክፈቻ ዝርዝር መረጃ አለመስጠት።
  • ለተጨማሪ መከላከያ ማግኘት መቻል – ከተቻለ ለእርስዎ ኦንላይን አካውንት እውነተኛ የሆነ ለብዙ-ነገር ማቀናጀት እና ለኦንላይን አካውንት ሲጠቀሙ በማንኛውም መሳሪያ ላይ ወቅታዊ የሆነ ጸረ-ቫይረስ ሶፍትወር ስለማስገባት ማረጋገጥ ነው።
  • መርበቦችን ማጣራት – ወብፓጅ/webpage የእርስዎን መክፈቻ መረጃ በሚጠይቅበት ጊዜ ‘ዩኒፎርም መገልገያ ማሳያ/Uniform Resource Locator’ ወይም ‘URL’ የሚባል ምን እንደሆነ ማስታወሻ መውሰድ። ይህ በእርስዎ ወብ ማውጫ ብራውዘር/browser አድራሻ ባር ላይ እንዳለ እና በተለይ በ ‘https://’ ይጀምራል
  • ሞባይል ፎን ስለማስገባት– ለሞባይል ፎን ለያዙ በጥንቃቄ መጠበቅ ያለበት፤ የእርስዎ ፎን ካሁን በኋላ ነትዎርክ/network ተቋርጧል የሚል ያልተለመደ መልእክት፤ ወይም ለእርስዎ ሞባይል ለያዘ እንዲቋረጥ መምሪያ እንዳልሰጡ ነው። ይህ በሚፈጠርበት ጊዜ ለሞባይል ፎንዎ ለያዘ ወዲያውኑ ጉዳዩን እንዲያስጠነቅቁ እንመክራለን።
  • ለማጭበርበሪያ ክትትል/Scamwatch መምሪያ ግምገማ – እርስዎን ከማጭበርበር ለመከላከል የአውስትራሊያ ውድድርና ተጠቃሚ ኮሚሽን በማጭበርበሪያ ክትትል ያወጣውን መመሪያ እንደገና ግምገማ እንዲደረግለት ይፈልጉ ይሆናል።

ስለርስዎ ማንነት መታወቅ መከላከል የበለጠ መመሪያ የሚፈልጉ ከሆነ የአውስትራሊያ ሳይበር ደህንነት ማእከልን መመሪያ ገጽ ላይ ገብቶ ማየት።

ስለ ችግሩ አፈጣጠር ሙሉ ሀሳብ እንዲኖርና ደንበኞችቻችን የተጎዱበትን መንገድ ለመረዳት አሁንም ጥንቃቄ ባለው ሂደት እያካሄድን ነው። ጠቃሚ የሆነ ወቅታዊ መረጃ በሚመጣበት ጊዜ፤ ማለት ማካሄድ በሚችሉት የጥንቃቄ እርምጃዎችን ያካተተ ወቅታዊ የሆነ ምክርን ልናቀርብልዎት ቃል ገብተናል።

በጭንቀት ምንፈስ የሚሰቃዩ ከሆነ ፈቃድ ካለው የተመዘገበ የሚያውቁትና የሚያምኑት ጤና ባለሙያ የጤና ምክር ማግኘት እንዳለብዎት እንመክራለን።

ተጨማሪ እርዳታ የት ማግኘት ይችላሉ?

ለእርስዎና ለሚወዱት ሰው ተጨማሪ እርዳታ የሚቀርበው በዚህ ችግር ፈጠራ ላይ በማንኛውም ጥያቄዎች ወይም አሳሳቢ ጉዳይ ላይ መፍትሄ እንዲገኝ ለመርዳት ነው። በነዚህ የሚካተት:

የአውስትራሊያ ቀይ መስቀል

ከዚህ በላይ በተጠቀሰው ስልክ ቁጥሮች በመጠቀም ለእኛ ሆትላይን መደወል ይችላሉ።

እንዲሁም እባክዎ በዚህ ቀጣይ ቀናት ወቅታዊ ለሆነ ይህን ወብፓጅ/webpage ላይ ማጣራት።

ለማንነት እንክብካቤ/IDCARE

ስለ ግላዊ መረጃዎ ያላግባብ መጠቀም ስለመቻል ካሳሰብዎት፤ ከ IDCARE፤ ከአውስትራሊያ አገር አቀፍ ማንነት እና ሳይብረስ ደህንነት ማህበረሰብ ድጋፍ አገልግሎት በነጻ እርዳታ እንዲያገኙ እናቀናጃለን።

ሰፋ ባለ የማንነት ደህንነት ጥበቃ ካሳሰብዎት እባክዎ ለ IDCARE ጉዳይ አስተዳዳሪ በ IDCARE’s እርዳታ ማስገኛ ወብ ቅጽ አድርጎ ተሳትፎ ግንኙነት ማድረግ።

በሌላ አማራጭ ደግሞ፤ ስለርስዎ ግላዊ መረጃ አጠባበቅ ለበለጠ መረጃ እና መገልገያዎች በIDCARE’s መማሪያ ማእከል ገብቶ ማየት። የIDCARE’s አገልግሎቶች ሊቀርቡ የሚችሉት “እርዳታ ማግኘት/Get Help” ወብ ቅጽን ካጠናቀቁ በኋላ በሚሰጥ የመላኪያ ኮድ ምልክት RCA-ID22 ወይም ሰልክ በመደውል: 1800 595 160

የእርስዎ ጤና ጥበቃ ባለሙያ

በጭንቀት የሚሰቃዩ ከሆነ ፈቃድ ካለው የተመዘገበ የሚያውቁትና የሚያምኑት ጤና ባለሙያ የጤና ምክር ማግኘት እንዳለብዎት እንመክራለን። የአጠቃላይ ህክምና ባለሙያ ሀኪምዎን በሚያዩበት ጊዜ፤ ምን እርዳታ እንደሚረዳዎ በምርመራ ያጣራሉ።

እነዚህ ድርጅቶች እንዴት ለእርስዎና ለሚወዱት ሰው መርዳት እንደሚችሉ ለበለጠ መረጃ እባክዎ ወደ እኛ ኢሜል ገብቶ ማየት።

Charity donations of $2 or more to Australian Red Cross may be tax deductible in Australia. Site protected by Google Invisible reCAPTCHA. © Australian Red Cross 2024. ABN 50 169 561 394